የሳይፈን አጠቃቀም

ሰይፈን ለAndroid

በመጀመሪያ የሳይፈን ለAndroid ቅዲዎ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ አለብዎት።

መጫንን ለማስጀመር የሳይፈን APK ትይይዝን ከAndroid ኢሜል ደምበኛ ላይ ወይም የድር መዳሰሻ ላይ ጠቅ ያድርጉ። (ስህተት ካገኙ የጎንዮሽ ጫኙን ማስቻል ሊያስፈልጎት ይችላል።)

የሳይፈን መተግበሪያን በሚያስጀምሩበት ወቅት ከሳይፈን ኔትወርክ ጋር መገናኘት በራሱ ይጀምራል።

Screenshot showing the Psiphon for Android status panel
 • ሳይፈን እየሰራ ያለው በVPN  ወይም የመሳሪያ ሙሉ በሙሉ ሁነታ ነው። ሁሉም መተግበሪያዎች የሚዘዋወሩት በሳይፈን አማካኝነት ነው።
 • የሁኔታ ትር ተመርጧል
 • ሳይፈንን በመሳሪያ ሙሉ በሙሉ ሁነታ መዘዋወሪያ ለማሰራት Android 4.0+ ወይም ሩትድ የሆነ መሳሪያ ሊኖርዎት ያስፈልጋል።

  ሩትድ ላልሆኑ የቆዩ የAndroid ስሪቶች ይህ አማራጭ አይገኝም ።
 • ግራጫ፡- በማገናኘት ላይ
  ቀይ፡- አልተገናኘም
  ሰማያዊ፡- ተገኛኝቷል
 • እየተጠቀሙ ያሉት የትኛውን የሳይፈን ስሪት እንደሆነ ያሳያል

Screenshot showing the Psiphon for Android logs panel
 • የሳይፈን እንቅስቃሴ መዝገብ

Screenshot showing the Psiphon for Android statistics panel
 • የግንኙነት ቆይታ
 • በሳይፈን በኩል የተላከ ዳታ
 • በሳይፈን በኩል የደረሰ ዳታ
 • በሳይፈን በኩል ታምቆ የተላከ ዳታ
 • በሳይፈን በኩል ታምቆ የደረሰ ዳታ

መተግበሪያው ከኔትወርኩ ጋር አንዴ ከተገናኘ አብሮ ገነብ የሆነውን የሳይፈን መዳሰሻ ያስጀምራል። የAndroid ሳይፈን ነባሪ የAndroid መዳሰሻን ወይም የሌሎች መተገበሪያዎች የኢንተርኔት ትራፊክን በራሱ አያዘዋውርም። በነባሪው በሳይፈን ኔትወርክ ውስጥ የሚተላለፈው የሳይፈን መዳሰሻ ብቻ ነው።

Screenshot showing the Psiphon for Android web browser
 • ሳይፈን እየሰራ ነው
 • የተከፈቱ ትሮችን ለዋውጥ
 • አሁን ያለውን ትር ዝጋ
 • የአሁኑ ገጽ ላይ እልባት አድርግ
 • አዲስ ትር ክፈት

ሰይፈን ለWindows

በመጀመሪያ የWindows ሳይፈን ቅዲዎ ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ አለብዎት።

የደምበኛውን ፕሮግራም በማውረድ ያስኪዱት። በሚያስኬዱበት ወቅት ይህ የሳይፈን ኩባንያ ትክክለኛ ምርት እንደሆነ የሚያሳይ የደንነት መግለጫ ማየት ይኖርቦታል።

Screenshot showing the Windows security warning for the Psiphon executable

ሳይፈንን ሲያስሰሩት በቀጥታ ግንኙነት መፍጠር ይጀምራል። በሚገናኝበት ወቅት የሚሽከረከር አዶ ይታያል። ከሚከተሉት የማዘዋወሪያ ሁነታዎች አንዱን መምረጥ ይችላሉ፡- VPN (L2TP over IPsec)፣ SSH ወይም SSH+ (SSH እና መሰወር ፣ የፕሮቶኮል አሻራ ለማስቀረት በSSH ላይ የተጨመረ የዘፈቀደ ንብርብር )።

Screenshot showing Psiphon starting up on Windows

አረንጓዴ አዶ ሲታይ ከሳይፈን አገልጋይ ግንኝነት መፈጠሩን ያመለክታል። በVPN ሁነታ ውስጥ ሁሉም የኢንተርኔት ትራፊክዎ በሳይፈን አማካኝነት በቀጥታ ይዘዋወራሉ።

በSSH and SSH+ ሁነታዎች ሳይፈን የWindows ስርአት ተኪ ቅንብሮችን በራሱ  ያስተካክላል። ይህም ይንን ስርአት የሚያከብሩ የመተግበሪያዎች ኔትወርክ ትራፊክ በሳይፈን ማስተላለፊያ ውስጥ እንዲያልፉ ያደርጋል። እነኚህ ቅንብሮች በሁሉም ዋና ዋና የድር መዳሰሻዎች በነባሪ ይከበራሉ።

በተጨማሪም በSSH እና SSH+ ሁነታዎች ውስጥ ሳይፈን የተከፈለ ማዘዋወሪያ አማራጭን ይሰጣል። ይህም አለማቀፍ ትራፊክ በተኪው አማካኝነት ሲዘዋወር የአካባቢ ትራፊክ ደግሞ በተኪው አይዘዋወርም። የተከፈለ ማዘዋወርያን ለማስቻል “የአካባቢ ድረገጾችን በተኪ አታድርግ” የሚለውን ይምረጡ። ይህ ምርጫ በሚመረጥበት ወቅት ያልተተኩ ጎራዎች በመልእክት ክፍሉ ይዘገባሉ ።

Screenshot showing Psiphon connected on Windows

ፕሮግራሙን በሚዘጉበት ወቅት ሳይፈን በራስሰር ግንኙነቱን ያቋርጣል። በተጨማሪም አዶው ላይ ጠቅ በመድረግ ግንኙነቱን መቀያየር ይችላሉ።