እኛ ማን ነን
የPsiphon ኢንክ. በቶሮንቶ የሚገኝ ኩባንያ ሲሆን በሳምት ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች የኢንተርኔት ይዘትን እንዲያገኙ የሚያደርግ ክፍተ ምንጭ የሆነ ብዙሃ አእማድ ሶፍትዌርን የሚሰራ ኩባንያ ነው። በምንችለው መጠን ምርጥ ሶትዌርን ለማቅረብ፣ በየጊዜው አዳዲስ ምርቶችን ለማስተዋውቅ እና ያለማቋረጥ እያደገ የመጣውን የአለም አቀፍ ታዳሚዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት የምንጥር ቡድን ነን።
አስፈጻሚ ቡድን
ማይክል ኸል የPsiphon ኩባንያ ፕሬዝዳንት ሲሆን Psiphon በቶሮንቶ ዩኒቨርስቲ የሲትዝን ላብ ውስጥ ፕሮጀክት ከነበረበት ወቅት ጊዜ አንስቶ ከPsiphon ጋር አብሮ የነበረ ነው። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ የሶፍትዌር መገንባት ጥረቶችን በመምራት ያገለገለ ሲሆን Psiphonን በውድድሩ ቀዳሚ እንዲሆን የሚያስችሉ ፈጠራዎችን አምጥቷል።
ሶፍትዌር መሥራት
በPsiphon ተጠቃሚዎቻችን መልካም ተሞክሮ እንዲኖራቸው እንፈልጋለን። ይህ ማለት ሶፍትዌራችን ለመጠቀም ቀላል፣ ኔትወርካችን ፈጣን እና ሁለቱም መሰረተ ጽኑ እና አስተማማን መሆን አለባቸው። ይህን ማሳካት በተለይም ሶፍትዌሩ ሁልጊዜም በለውጥ ላይ ባለ አስቸጋሪ ከባቢ ውስጥ እና በብዙ ቋንቋዎች እና አእማዶች መስራት በሚጠበቅበት ወቅት ለማንኛውም የሶፍትዌር አበልጻጊ በቀላሉ የሚቻል አይደለም።
ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆኖ ጠንክሮ መስራት ለተጠቃሚዎቻችን አስፈላጊ እንደሆነ እንረዳለን። ተጠቃሚዎቻችንን እና ዳታዎቻቸውን በምንችለው አቅም ሁሉ እንጠብቃለን። ተጠቃሚቆች ግላዊነታቸውን እና ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ የምንወስዳቸውን እርምጃዎች ላያስተውሉ ይችላሉ ነገር ግን እንደሚያደንቁት እናውቃለን።
የPsiphon ሶፍትዌር አበልጻጊ ቡድን ምርጥ፣ ፈጣን፣ ቀላል እና ክፍት የማለፊያ መፍትሄዎችን ለማቅረብ ይተጋል። በተጨማሪም በአለም ላይ ያሉ ተጠቃሚዎችን አእምሮ ነጻ የሚያወጡ፣ የሚጠብቁ እና ብቃትን የሚጨምሩ በሙያችን ያሉ አዳዲስ ነገሮችን ለማየት እንሞክራለን።
- Wesley Cranston
- Rosalind Deibert
- Mike Fallone
- Eugene Fryntov
- Michael Goldberger
- Rod Hynes
- Imran Iqbal
- Draven Johnson
- Amir Khan
- Adam Kruger
- Miro Kuratczyk
- Tasker Mackersy
- Enda O'Monahan
- David Osborne
- Adam Pritchard
አፈጻጸም እና የህዝብ ግንኙነት
ከትልልቅ አለማቀፍ አስተላላፊ ኩባንያዎች እስከ በአንድ ሃገር ብቻ የሚሰሩ ትንንሽ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ድረስ ከብዙ ኩባንያዎች ጋር የስራ ስምምነቶች አሉን። የአፈጻጸም እና ህዝብ ግንኙነት ቡድናችን ስንት ሰዎች በስርጭት መንገዳቸው አማካኝነት Psiphonን እንደሚጠቀሙ ሪፖርቶችን በማዘጋጀት ያሳያሉ። በተጨማሪም በኢንተርኔት ላይ ነጻ የመረጃ ስርጭት ላይ ተጽኖ ሊያሳድር የሚችሉ ሁኔታዎችን እና ሁነቶችን አዝማሚዎች በማየት ጥናት ያደርጋሉ።
አጋርነቶች
Psiphon በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ Psiphon ን ለሚጠቀሙ ሰዎች ድጋፍ እና ምክር ለመስጠት ከተለያዩ ቡድኖች ጋር በቅርብ ይሠራል ፡፡ ለሶፍትዌራችን በብዙዎች ቋንቋዎች ትርጉሞች አለን ፣ እና በትርጉም ልኬታችን እገዛ በ Transifex በኩል ወደ ምርታችን የበለጠ እየጨመርን ነው።